
ኢትዮሞኒተር፡ 27/10/2017፡ የአሜሪካ ወታደሮች ከአራት ዓመታት በፊት ሀገሪቱን ለቀው በወጡበት ወቅት ሥልጣኑን ከተቆጣጠረው የታሊባን ባለስልጣናት ጋር ወዳጅነት ለመመሥረት በሚደረገው ጥረት ሩሲያ የአዲሱን የአፍጋኒስታን አምባሳደር የሹመት ደብዳቤ ተቀብላለች።
የሩስያ ውጪ ጉዳይ ሚኒቴር ትላንት ባወጣው መግለጫ “ከአፍጋኒስታን ጋር በኢነርጂ፣ በትራንስፖርት፣ በግብርናና መሠረተ ልማት መስኮች ላይ የንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር ማድረግ የሚቻልበት ዕድልን እየተመለከተች ነው” ሲል ገልጿል።
እንዲሁም ሞስኮ ቀጣናዊ ፀጥታን በማጠናከር ሽብርተኝነትን እና ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ የካቡል መንግሥትን መርዳቷን እንደምትቀጥል አመላክቷል፡፡
ይህም እርምጃ ሩሲያ በዓለም ላይ የሀገሪቱን የታሊባን መንግሥት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር አድርጓታል።