
ኢትዮሞኒተር፡ 26/10/2017፡ ሱዳን ፋውንዲንግ አሊያንስ በሚል የተመሰረተው ጥምረት ትላንት በሰጠው መግለጫ በይፋ ምስረታውን ማከናወኑን አስታውቋል፡፡
በኒያላ ግዛት ውስጥ ባከናወነው ምክክር 31 የምክር ቤቱን አመራሮች መምረጡን አስታውቆም ምክር ቤቱን በሊቀመንበርነት እንዲመሩ ጄኔራል ሀምዳን ዳጋሎ መመረጣቸውን አስረድቷል፡፡ በምክር ቤቱ ውስጥ ያሉት ሌሎች አባላት ከተለያዩ ፓርቲዎች፣ ታጣቂ ቡድኖችና ሲቪል ድርጅቶች የተውጣጡ መሆናቸውን ገልፆም በቅርቡ በቁጥጥራቸው ባሉ ቦታዎች ላይ “የሰላምና የአንድነት መንግስት” እንደሚመሰርት አስታውቋል፡፡
ይህ መንግስት በጄኔራል መሀመድ ዳጋሎ እንደሚመራና 15 አባላት ያሉት የፕሬዝደንት ምክር ቤት እንደሚኖረው ጠቅሶ በጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ካቢኔ እንደሚኖረውም አስረድቷል፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ጦርነት ለማስቆም የሚደራደረውም ይህ መንግስት እንደሚሆን ገልፆ ዝርዝር ጉዳዮችን እንደሚያሳውቅ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ጥምረት ከወራት በፊት የተመሰረተው በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡