ኢትዮጵያፖለቲካ

በትግራይ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ኤምባሲዎችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው “በፍጥነት” ሚናቸውን እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ።

ኢትዮሞኒተር፡ 26/10/2017፡ የትግራይ ክልል “ወደ ጦርነት እንዳይገባ” የሃይማኖት አባቶች፣ ባለሃብቶች፣ ምሁራን እና ኤምባሲዎች ሚናቸውን “በፍጥነት” እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ በፓርላማ ተገኝቶ በሰጡት ማብራርያ ጥሪ አቀርቧል።

በትግራይ ውጊያ ከተጀመረ፤ ከዚህ በፊት ከነበረው የተለየ እንደሚሆንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስጠነቀቁት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ የተመለከተው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት አንድ  የትግራይ እና ኤርትራን የተመለከቱት ጉዳዮች አንስቷል።

“የትግራይ ህዝብ መቶ ፐርሰንት ጦርነት አይፈልግም” ያሉት አብይ፤ ከህዝብ ፍላጎት እና አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ ውጭ በክልሉ ውጊያ ቢቀሰቀስ “ዓለም ደንታ የለውም” ብለዋል። “[ዓለም] ብዙ ውጊያ እያስተናገደ ስለሆነ፤ ጆሮም የለውም፣ ጊዜም የለውም። ዓለም ጊዜ ቢኖረው ኖሮ ሱዳንን ያዳምጥ ነበር” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተደምጠዋል።
አሁንም ተራራና ሜዳን የሚያስቡ ሰዎች አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጦርነት ስልቱ ተቀይሯል እስራኤልና ኢራን በተራራና ሜዳ አይደለም የተዋጉት ብሏል። መንግስት እዚህም እዛም ተወጥሯል ለሚሉም ውጊያው ሰራዊት በማሰለፍ ብቻ እንደማይካሄድ ጠቁሟል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates