ዲፕሎማሲ
“የኢትዮጵያ መንግስት ኤርትራ ላይ አንድም ጥይት አይተኩስም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ገለፁ።

ኢትዮሞኒተር፡ 26/10/2017፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዛሬ ከምክር ቤት አባላት ከተነሱላቸው ጥያቄዎች አንዱ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያላት ግንኙነት የተመለከተ ነው።
ባለፉት 7 ዓመታት ከአንድም ጎረቤት አገር ውግያ ውስጥ አልገባንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኤርትራ ጋርም ወደ ጦርነት አንገባም ብልዋል። “እሮግጠኛ ሆኜ የምናገረው በኛ ወገን ወደ ኤርትራ አንድ ጥይት አንተኩስም” ያሉት ዶ/ር አብይ የጎረቤት አገራት ማወቅ ያለባቸው ግን ኢትዮጵያ በትናንሽ ጠጠር አትታወክም” ብሏል።
“ኤርትራ ሉአላዊ አገር ናት፣ በግድ የኢትዮጵያ አካል እንድትሆን እኛ አንፈልግም። ጅቡቲ ሉአላዊ ሀገር ናት፣ መከበር አለባት። ሶማሌያ ሉአላዊ ሀገር ናት፣ መከበር አለባት። ጥያቄ የለንም። ኢትዮጵያ ሉአላዊ አገር ናት የባህር አክሰስ ካላገኘች ግን ሀገር መሆን አትችልም። በነሱ ወገን በኩል ደግሞ ይህ መከበር አለበት” ሲሉ ተናግሯል ዛሬ በፓርላማ የተገኙት ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ አህመድ።