አፍሪካ
በሶማሊያ ወታደራዊ አውሮፕላን ተከሰከሰ።

ኢትዮሞኒተር፡25/10/2017፡ ዛሬ ማለዳ ላይ የዩኤስ ጦር ለዳናብ ሃይል ስልጠና ከሚሰጥበት ከባሊዶግሌ አየር ማረፊያ የተነሳው አውሮፕላን በሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ መከስከሱ ጋርዎይ ኦንላይን ዘግበዋል።
በአውሮፕላኑ ውስጥ 8 ሰዎች እንደነበሩ የጠቆመው ዘገባው በህይወት ስለመኖራቸውና አለመኖራቸው ግን ያለው ነገር የለም፡፡
“እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ጉዳት ደርሶባቸው ወይም ደህና መሆናቸውን አናውቅም” ሲል የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር አህመድ ማካሊን ሀሰን ገልፀዋል፡፡
አውሮፕላኑ የአፍሪካ ህብረት ሃይሎች በተለይም የኡጋንዳ ወታደሮች እንደነበሩበት ተጠቁመዋል።