አፍሪካፖለቲካ

የሱዳኑ መሪ አብደልፈታህ አልቡርሃንና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ መገናኘታቸው ተገለፀ፡፡

ሁለቱም መሪዎች የተገናኙት በካይሮ ከሊቢያው ወታደራዊ አዛዥ ካሊፋ ሃፍታር ከተወያዩ በኃላ ነው ተብለዋል፡፡

ኢትዮሞኒተር፡25/10/2017፡  የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ አብዱልፈታህ አልቡርሃን ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ጋር በካይሮ ሰኞ እለት ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች መወያየታቸው ሱዳን ትሪቡን ዘግበዋል፡፡

የሁለቱ መሪዎች ግንኙነት የግብፅ መሪ አልሲሲ ከሊቢያው አዛዥ ከሊፋ ሃፍታር ጋር የተለየ ውይይት ካደረጉ ከሰአታት በኋላ የተደረገ መሆኑም መረጃው ጠቁመዋል፡፡ አልቡርሃን በስፔን እየተደረገ ከሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ኣቋርጠው ወደ ካይሮ ያቀኑ ሲሆን ምክንያቱም ከካሊፈ ሃፍታር ለመወያየት መሆኑ ተገልፀዋል፡፡

ካሊፋ ሃፍታር የሱዳኑ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ታጣቂ ቡድንን እንደሚደግፉ የሱዳን መንግስት ሲከስ መቆየቱ ይሚታወስ ነው፡፡ በዚህ ቡድኑ በሃፍታር ድጋፍ ወሳኝ ስትራቴጂክ ቦታ የሆነው የሊቢያ፣ ሱዳንና ግብፅ ድምበር መያዙን ይታወሳል፡፡ ውይይቱን የሚያውቁ ሁለት ምንጮች ሲሲ የድንበር ውጥረቱን ለማርገብ ቡርሃን እና ሃፍታር  ለማስታረቅ ሊፈልግ እንደሚችል ተናግረዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates