
ኢትዮሞኒተር፡ 24/1/2017፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ሀገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የመሆን መብት አዋጅን አጸደቀ።
መሬት የመንግስት እና የህዝብ እንደመሆኑ ለኢንቨስትመንት የሚመጡ ዜጎች መሬቱን የመሸጥ እና የመለወጥ መብት የላቸውም ተብለዋል።
የኢትዮጵያዊያንን መብት በማይነካ መልኩ የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖርያ ቤት ባለቤት በመሆን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ሥራዎች ይሰራሉ ነው ያለው ቋሚ ኮሚቴው።
የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ነው።
የቀረበው የገንዘብ መጠን አነስተኛ መሆኑ የተነሳ ሲሆን የተቀመጠው የገንዘብ መጠን አሁን በኢትዮጵያ ካለው የቤት ገበያ ጋር በማነፃፀር የወጣ ስለመሆኑም ተብራርቷል።
የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ሲሆን በጊዜ ሂደት ግን እየተሻሻለ እንደሚሄድም ተመላክቷል።