
ኢትዮሞኒተር፡ 24/1/2017፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 41ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ በ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ፤ ማክሮ ኢኮኖሚው የተረጋጋ የሚሆነው የመንግስት ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ሲያድግ ነው።
አዲስ የፋይናንስ ሥርዓት ነው የያዝነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ በከፍተኛ ጉዳይ ገቢያችንን ማሳደግ የሞት የሽረት ጉዳይ ነው ብለዋል።
ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸር ታክስ ለጥቅል አገራዊ ምርት ያለው ምጣኔ ዝቅተኛ ነው፤ ይህንን በቀጣይ አራት ዓመታት በ4 በመቶ ማሳደግ ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።