ኢትዮጵያዲፕሎማሲ

የህወሓት ህጋዊነት በምርጫ ቦርድ መሰረዝ ችግር ይፈጥራል ሲሉ ጀኔራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ፡፡

ጄነራል ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር ለመወያየት ማሰባቸውን ተናገረዋል፡፡

ኢትዮሞኒተር፡ 20/10/2017፡ የህወሓት ህጋዊነት በምርጫ ቦርድ መሰረዝ ችግር ይፈጥራል ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጀኔራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ከጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር በመገናኘት ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማስቻል እና “በወራሪ ሀይሎች” የተያዙ የክልሉ አካባቢዎችን ነጻ ማውጣት በሚሉ አጀንዳዎች ዙሪያ ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚወያዩ አስታውቀዋል።

ሌተናል ጀነራል ታደሰ “በክልሉ እያጋጠሙ ያሉ ተደጋጋሚ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከፌዴራል መንግስት ጋር የፖለቲካ ውይይት እንዲደረግ እንጠይቃለን” ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት በተባበሩት መንግስታት ደርጅት የልማት ፕሮግራም የአደጋ እና ዝግጁነት ቢሮ ምክትል ዳይሬክተር ቱርባን ሳሌህ የተመራ ልዑክን ትናንት ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

ፕሬዝዳንቱ ከልዑካኑ ጋር በነበራቸው ውይይት፤ “ወደ ጦርነት እንድንገባ የሚያደርገን ምክንያት የለም” ሲሉ ገልጸው “ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እና የክልሉን የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ ከፌደራል መንግስት ጋር በቀጣይ ተቀራርቦ መስራት ያስፈልጋል” ማለታቸውን ከጽ/ቤታቸው ያገኘነው መረጃ የሳያል። የፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት በመረጃው እነዚህን አጀንዳዎችንም ቅድሚያ ሰጥተው በቀጣይ ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር እንደሚወያዩ ቢያስታውቅም ውይይቱ መች እንደሚደረግ አልገለጸም።

በሌተናል ጄኔራል ታደሰ እና በኢትዮጵያ ከተመድ ልማት ፕሮግራም ልዑካን ቡድን መካከል የተደረገው ውይይት በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ እና በፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ዙሪያ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ጽ/ቤቱ ጠቁሟል።

ፕሬዝዳንቱ ለልዑኩ “የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን” ገልጸው፣ “ፓርቲው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚ በመሆኑ ችግር እንዳይፈጠር በአፋጣኝ ከፌዴራል መንግስት ጋር ፖለቲካዊ ውይይት በማካሄድ መፍትሔ እንዲያገኝ መስራት አስፈላጊ መሆኑን እንዳስገነዘቡ ጽ/ቤታቸው በመረጃው አመላክቷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates