ኢትዮጵያፖለቲካ

የትግራይ ህዝብ የህልውና አደጋ ተጋርጦበታል ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ፡፡

"በአምስት ሰነፎች የተነሳ የትግራይ ሕዝብ ለጦርነት መማገድ መቆም አለበት" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ኢትዮሞኒተር፡ 20/10/2017፡ ‘አንድ ፖርቲ ውስጥ ያሉ አምስት ሰነፎች’ ሲሉ የጠሯቸው ግለሰቦች፤ የትግራይን የህልውና ችግር ውስጥ ከተውታል ሲሉ አቶ ጌታቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ይህንን ያሉት center for responsibility and peaceful politics የተሰኘ ድርጅት በአዲስ ኣበባ ባዘጋጀው ውይይት ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው። ድርጅቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ሰላም፣ ዲሞክራሲ እና ልማት በትግራይ እድሎች እና ፈተናዎቸ በሚል ርዕስ ውይይት ኣካሂደዋል።

በዚህ የውይይት መድረክ ላይም አቶ ጌታቸው ረዳ እና የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስን ጨምሮ በርካታ የተለያዩ ፖለቲካዊ አቋም ያላቸዉ የትግራይ ፖለቲከኞችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ተገኝተዋል። በውይይት መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ጌታቸው ረዳ፤ “አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ የትግራይ ሕዝብ ሰላም ያስፈልገዋል” ያሉ ሲሆን፤ “ሕዝቡ አሁን የህልውና አደጋ የተጋረጠበት ሆኗል” ሲሉ ገልጸዋል።

“አሁን የትግራይ ሕዝብ ልማት ይቆይለት” ያሉት አቶ ጌታቸው፤ “መልማት ችግር የለውም ግን ሕዝቡ የህልውና አደጋ ተጋርጦባታል” ብለዋል። “አምስት እና ሰባት የሆኑ ሰነፎች የትግራይ ህዝብንና ወጣቱን ወደ ጦርነት የሚማግዱበት ሁኔታ መቆሞ አለበት! ለዚህ ደግሞ ዲሞክራሲ የግድ ይላል” ሲሉም ተደምጠዋል። እነዚያ አምስትና ሰባት ያሉዋቸው ሰነፎች ግና እነማን መሆናቸው አልጠቀሱም፡፡

የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሀመድ እድሪስ በበኩላቸው “በትግራይ ፖለቲካም ሆነ በሀገሪቱ ያሉ የፖለቲካ ሂደት ላይ በአብዛኛው ከፊት ወጣቶች አይመጡም” ብለዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ ውይይት ግን ወጣቶችን ወደ ፊት ለማምጣት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

“በትግራይ ፖለቲካ ውስጥ ይህ የዛሬው ወይይት ታሪካዊ የሆነ ውይይት እንደሚሆን አልጠራጠርም” ሲሉም ተናግረዋል። “ጦርነት ይበቃ ለማለት ድፍረት ይጠይቃል” ያሉት ሚኒስትሩ፤ “ሰላም ማለት ድፍረት ይጠይቃል፤ ከጦርነት የሚያተርፍ ሕዝብ የለም” ሲሉ ገልጸዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates