
ኢትዮሞኒተር፡ 20/10/2017፡ ኢትዮጵያ “ግጭት ለመቀስቀስ እና ምክንያታዊ ለማስመሰል” ዲፕሎማሲያዊ መልዕክቶችን እየተጠቀመች ነው ስትል ኤርትራ ከሰሰች
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ትናንት ሰኔ 19 ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ቀናት “የዲፕሎማሲያዊ ዘመቻዎችን አጠናክሯል” ሲል ገልጾ፤ መልዕክቶቹ ፤ “እያየለ በመጣው የጦርነት አጀንዳው ላይ ድጋፍ ለማግኘት የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳመን ያለመ ግልፅ ዘዴ ነው” ሲል ከሷል።
የኢትዮጵያ መንግስት ኤርትራን “በኢትዮጵያ ላይ ትንኮሳ በመፈጸም “ እና “ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን በመጣስ” ለመክሰስ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ እና ለበርካታ ሀገራት መንግስታት ዲፕሎማሲያዊ መልዕክቶችን ልካለች ሲል የኤርትራ መንግስት ቅሬታ አሰምተዋል። ይህም “ግጭት ለመቀስቀስ እና ምክንያታዊ ለማስመሰል የሚደረግ ጥረት አካል ነው” ሲል ነው
የኤርትራ መንግስት ገዥው የብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ “አላስፈላጊ መግለጫ በማውጣት” እና “ወታደራዊ ማስፈራሪያ በመፈጸም ” ላይ ይገኛል ያለው የኤርትራ መግለጫ፤ እነዚህ እርምጃዎች የኤርትራ ወደቦችን “ከተቻለ በህጋዊ መንገድ ካልሆነም በወታደራዊ ኃይል” ለመያዝ የሚያደረገው “ሰፊ ስትራቴጂ ጥረት አካል ናቸው” ብሏል።
እንደ የኤርትራ መንግስት ገለጻ፤ እነዚህ ድርጊቶች “በርካታ የጦር መሳሪያ ግዥዎችን ” እና “መንግስትን የማዳከም በርካታ ጥረቶችን” ያካተቱ ናቸው። “ምንም እንኳን እነዚህ ድርጊቶች ለኤርትራ ሉዓላዊነትና ግዛታዊ አንድነት እንዲሁም ለቀጠናው መረጋጋት ከባድ ስጋት ቢጥሉም፤ ኤርትራ በትዕግስት እያለፈችው ትገኛለች” ብሏል።
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ላይ ያቀረበውን ክሶች ለመድገም ሲል “እውነታዎችን አዛብቷል” ሲል ከሷል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ መንግስታት “ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል በርካታ የኤርትራ ሉዓላዊ መሬቶች በሕገወጥ መንገድ ተይዞ መቆየቱን” ገልጿል። ይህም “የዓለም አቀፍ ህግ፣ የተባበሩት መንግስታት ቻርተር እና የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ማካለል ኮሚሽን ስምምነት ጥሰት ነው” ብሏል።
ይህ የኤርትራ መግለጫ የተሰጠው፤ ትክክለኛነቱ ያለተረጋገጠ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤ በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን ተከትሎ ነው።
ከዚህ በፊት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ነበር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እና ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ የኤርትራ ትንኮሳ የተመለከተ ፅሑፎች እንዳሰራጩ ይታወሳል፡፡