ቱሪዝምኢትዮጵያ

በትግራይ ክልል የታሪካዊው አል-ነጃሺ መስጂድ እድሳት ሥራ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/10/2017፡  በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ታሪካዊው የአል ነጃሺ መስጂድ የእድሳት ሥራ መጠናቀቁን የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

መስጂዱ ላለፉት 9 ወራት እድሳት ሲደረግለት ቆይቷል፡፡ የእድሳት ሥራውም ከቱርክ ልማት ኤጀንሲ በተገኘ ድጋፍ መከናወኑን ለማወቅ ተችለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከመስጂዱ የተዘረፉ ቅርሶችን ቁጥር የማጣራት ሥራ እየተሰራ እንደሆነም ቢሮው ገልጸዋል።

ከአፍሪካ ጥንታዊ እስላማዊ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የአል-ነጃሺ መስጂድ ጥልቅ ታሪካዊ እና ባህላዊ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን እድሳቱ ማጠናቀቁ የቱሪዝም ዘርፉ ከጦርነት ውድመት ዕድል እንደሚፈጥርለት ይገመታል፡፡

በትግራይ ክልል ከዉቅሮ 11 ኪሎ ሜትር ከአዲስ አበባ 800 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘዉ አልነጃሺ መስጂድ በእስለምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠዉ ታሪካዊ መስጂድ መሆኑ ይታወቃል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates