ኢትዮጵያኢኮኖሚ

ብሔራዊ ባንክ 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደገጠመው በገለልተኛ ኦዲት ተረጋገጠ ፡፡

 በዚሁ ዓመት በነበረ የብር መዳከም 38 ቢሊዮን ብር መክሰሩ ተገልጿል ፡፡

ኢትዮሞኒተር፡ 19/10/2017፡ እ.ኤ.አ. በ2024 ብሔራዊ ባንክ 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደገጠመው በገለልተኛ ኦዲት ተረጋገጠ ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ. በ2024 በአጠቃላይ የባንክ ሥራው 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደገጠመው በገለልተኛ ኦዲት ተረጋገጠ፡፡

ብሔራዊ ባንክ በገለልተኛ የውጭ ኦዲተር ኦዲት እንዲደረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት የተቀጠረው ኤምኤስኢ ኦዲት ሰርቪስ ኤልአልፒ (MSE Audit Service LLP)፣ የብሔራዊ ባንክን የ2024 የፋይናንስ እንቅስቃሴ ኦዲት በማድረግ ግኝቱን ይፋ አድርጓል፡፡

የኦዲት ሪፖርቱ በተያዘው ሰኔ ወር መጀመሪያ አካባቢ በብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ የባንኩን የዳይሬክተሮች ቦርድ በመወከል ተረጋግጦ መውጣቱን በሰነዱ መጀመሪያ ገጽ ላይ ተመላክቷል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ወርቅ የገዛበትና የሸጠበት ዋጋ ልዩነት መስፋት፣ ባንኩ ለመንግሥት አበድሮ መመለስ ያልቻለው (Impairment Loss) እንዲሁም በዚህ ዓመት የነበረው የብር የመግዛት አቅም መዳከም የተነሳ 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰው ሪፖርተር ዘግበዋል፡፡

በተመሳሳይ የውጭ ምንዛሪ በገበያ ዋጋ እንዲመራ ከመወሰኑ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 2024 በፊት በነበረው የብር የመግዛት አቀም መዳከም የተነሳ ብሄራዊ ባንክ 38 ቢሊዮን ብር መክሰሩን የኢዲት ሪፖርቱ አመልክተዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates