
ኢትዮሞኒተር፡ 19/10/2017፡ የዓለም ምግብ ፕሮግራም(WFP) በትግራይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የተፈናቃዮች ማቆያ በሆነው ሽሬ ከተማ የሚገኘው ፀ/ቤቱ ነው እንደሚዘጋ ያስታወቀው፡፡ የሚዘጋበት ምክያትም የበጀት እጥረት እና አሰራርን መልሶ ለማዋቀር እንደሆነ ተገልፃል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የአለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ በሽሬ፣ በክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው እና የተፈናቃዮች ብዛት በማስተናገድ ላይ የሚገኘውን ጊዝያዊ መጠሊያ በበጀት እጥረት ምክንያት እንደሚዘጋው አስታውቀዋል፡፡
የWFP የትግራይ አካባቢ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሌቫን ቻቹዋ “የሽሬ ጽህፈት ቤቱን እየዘጋን ነው” ነገር ግን “በሰሜን ምዕራብ ዞን ከመቀሌ ሆኖሥራችንን ማስተዳደር እንቀጥላለን” ብለዋል:: የእርዳታ መከፋፈሉን ኃላፊነት መንግስታዊ ላልሆነ የአሜሪካው ድርጅት ጥምረት ለጋራ የአደጋ ጊዜ ኦፕሬሽን (ጄኦፒ) እንደተሰጠ የገለፁት ሃላፊው የአለም ምግብ ፕሮግራም ግን “የአመጋገብ፣ የትምህርት ቤት ቀለብ እና የመቋቋም አቅም ያላቸውን ፕሮጀክቶች” መተግበሩን ይቀጥላል ብለዋል።
የአለም ምግብ ፕሮግራም ኢትዮጵያ ቃል አቀባይ ክሌር ኔቪል ውሳኔው በትግራይ፣ አማራ እና አፋር የሚካሄደውን የምግብ እርዳታ ወደ ጂኦፒ ለመመለስ “በ2024 መጨረሻ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከለጋሾች ጋር በመስማማት የተጀመረውን የሽግግር ምዕራፍ አካል ነው” ብለዋል። እንደ ኃላፊዋ ገለፃ የስራው ርክክቡ በዚህ ወር መጨረሻ ይጠናቀቃል፡፡
የሽሬው ቢሮ መዘጋት “የእኛን የስራ ሃይል አሁን ካለንበት የስራ አፈፃፀማችን መጠን እና ስፋት ጋር ለማጣጣም አስፈላጊ እርምጃ ነው” ሲሉ ቃል አቀባይዋ ተናግርዋል፡፡ አክለውም WFP “በትግራይ ውስጥ ከ280,000 በላይ ህጻናትን፣ እናቶችን እና አነስተኛ አርሶ አደሮችን በተለያዩ እርምጃዎች እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ድርጅቱ ከሽሬ በተጨማሪ በሶማሌ ክልል ቀብሪ ደሃር የሚገኘውን ቢሮውን ሊዘጋ እንደሆነ አስታውቀዋል።
ኤጀንሲው በሚያዝያ ሰጥቶት በነበረው መግለጫው “በየካቲት ወር ከመደበኛው የራሽን መጠን ወደ 65 በመቶ ዝቅ እንዲል ለማድረግ ተገድጃለሁ” ብሎ እንደነበር የሚታወስ ነው። bአሁን ጊዜ “9 ኪሎ እህል፣ 1 ኪሎ ጥራጥሬ እና 1.1 ኪሎ ግራም ዘይት” ያካተተ ነው።
ኤጀንሲው ቀደም ሲል ከግንቦት ወር ጀምሮ ለ650,000 በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለተጎዱ ሴቶች እና ህጻናት የሚሰጠውን የስነ-ምግብ መርሃ ግብሮች ማቋረጡን ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት የወለደው እንደሆነ ገልጿል።