
ኢትዮሞኒተር፡ 19/10/2017፡ የእሳት ቃጠለው በአፅቢ ወረዳ የዓፋር አዋሳኝ አከባቢ ነው፡፡
የትግራይ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ለፌደራል የአደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን በደብዳቤ እንዳስታወቀው ፤ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወረዳ ቃልአሚን ቀበሌ ሓይለ-ቡሐለ ልዩ ቦታ በሚገኘው የዱስኣ ጥብቅ ደን የእሳት ቃጠሎ አጋጥሟል።
“በዓፋር ክልል ልዩ ቦታ ገረብ ዋሕለ የጀመረው ቃጠሎ በሃይለኛ ንፋስ እየተስፋፋ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል ” ብሏል። “የአከባቢው ማህበረሰብ ቃጠሎው በባህላዊ መንገድ ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል ” ያለው ኮሚሽኑ ” ባለው ደረቅ የአየር ሁኔታና ሃይለኛ ንፋስ እየተባባሰ የከፋ ጉዳት በማድረስ ላይ ነው ” ሲል ገልጿል።