ኢትዮጵያኢኮኖሚ

ኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉን ለውጪ ባንኮች ክፍት ማድረጓን  አስታወቀች።

ኢትዮሞኒተር፡ 19/10/2017፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ለመክፈት የሚያስችለውን መመሪያ አጽድቋል።

ባንኩ፥ መመሪያ ቁጥር SBB/94/2025 ወይም “የባንክ ሥራ ፈቃድ፤ የእድሳት መስፈርቶች እና የውክልና ቢሮ መመሪያ ” መጽደቁን ነው ያስታወቀው።

በዚህ መመሪያ መሰረትም ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ባንኮችን ጨምሮ ሌሎች ስትራቴጂክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ ፈቅደዋል።

ብሔራዊ ባንክ ትላንት ባወጣው መግለጫ ፥ ” የኢትዮጵያ የባንክ መስክ ለውጭ ኢንቨስተሮች ተከፍቷል፤ የውጭ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች ማመልከቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ ይችላሉ ” ብለዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates