
ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/10/2017፡ እስራኤል የሚደረግላት ሁሉም ድጋፍ እንደምትቀበል አስታወቀች።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ” እንደሚወስኑ በመግለፅ ዩናይትድ ስቴትስ በጦርነቱ ውስጥ የመሳተፍ እድሏ በመቀነሱ እስራኤል ሐሙስ ዕለት የኢራንን የኒውክሌር ቦታዎችን ለመምታት “የሚደረግላትን ድጋፍ ሁሉ” እንደምትቀበል አስታውቃለች።
የኢራን ሚሳኤል ሐሙስ ዕለት የእስራኤልን ሆስፒታል ከተመታ በኋላ ቴህራን የጦር እና የስለላ ጣቢያን ኢላማ አድርጓል በተባለው ጥቃት፣ የመከላከያ ሚኒስትር እዝራኤል ካትዝ በኢራን መሪ ላይ ዛቻ ሰንዝረዋል፣ ይህም ለአንድ ሳምንት በዘለቀው ጦርነት ውጥረቱ እንዲጨምር አድርጓል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ኢራን በደቡባዊ ቤርሳቤህ ከተማ በሚገኘው የሶሮቃ ሆስፒታል በፈፀመችው ጥቃት 40 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው በመግለፅ “ኢራን ከባድ ዋጋ ትከፍላለች” ብለዋል። ኔታኒያሁ ትላንት በቴሌቭዥን ባስተላለፉት መልእክት አስራኤል “ሁሉንም የኢራን የኒውክሌር መስሪያ ቤቶችን መምታት ትችላለች” ነገር ግን “የሁሉም እርዳታ ትቀበላለች” ብለዋል። ይህ የድጋፍ ጥሪ እስራኤል ጦርነቱ እንደከበዳት ማሳያ ነው የሚሉ አሉ።