ኢትዮጵያፖለቲካ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ተወያዩ

ኦነግ እና ኦፌኮ በውይይቱ አልተሳተፉም ተብሏል።

ኢትዮ ሞኒተር፡12/10/2017፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትላንት ረቡዕ ሰኔ 11 ቀን ከተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር መወያየታቸውን አስታወቁ። ይሁን እንጂ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በውይይቱ ላይ አለመሳተፋቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል።

በውይይቱ እንዲሳተፉ ጥሪ የደረሳቸው ፓርቲዎች በሙሉ አራት ተወካዮችን እንዲያሳትፉ እድል ቢሰጣቸውም፤ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጥሪውን ውድቅ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር #መራራ_ጉዲና ፓርቲያቸው በውይይቱ ላይ አለመገኘቱን ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል። ፕሮፌሰር መራራ ምክንያቱን ሲገልጹም፤ “እንዲህ ያለው የማስመሰል ፖለቲካ እና በማይግባቡ አካላት መካከል የሚደረግ ውይይት አሁን ካለው የፖለቲካ ትርምስ ያወጣናል ብለን አናምንም” ብለዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ቃል አቀባይ አቶ ለሚ ገመቹም፤ ፓርቲያቸው በድርድር ከመሳተፍ መቆጠቡን ለአዲስ ስታንዳርድተናግረዋል።

በውይይቱ ከተሳተፉ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው ኢሕአፓ “ጥያቄ የመጠየቅ ዕድል አላገኘሁም፣ በሌሎች ፓርቲዎች የቀረቡ ጥያቄዎችም መሠረታዊ አይደሉም” በሚል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ከመስጠታቸው በፊት ተወካዮቹ መድረክ ረግጠው መውጣታቸውን ማስታወቁን ዶቼ ቬሌ ዘግቧል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates