ኢትዮጵያፖለቲካ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በቅርብ ጊዜ የተመሰረተውን ስምረት ፓርቲን በትግራይ ክልል እንዲንቀሳቀስ ትእዛዝ ሰጠ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/10/2017፡ ምርጫ ቦርዱ ለጊዝያዊ አስተዳደሩ በፃፈው ደብዳቤ ፓርቲው በትግራይ ክልል ውስጥ በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎች፣ ከተሞችና ቀበሌዎች ተንቀሳቅሶ አባላትን ለመመልመል እንዲችል ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የትብብር ደብዳቤ እንዲፃፍለት ጥያቅ ማቅረቡን ጠቅሷል፡፡
የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ  “በመሆኑም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተረዳደር የዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ(ስምረት) መስራቾች ፓርቲውን ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ለማከናወን ይረዳቸው ዘንድ በትግራይ ክልል ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው በአክብሮት እናሳስባለን” ብሏል፡፡
ከህወሓት ከወጡ በእነ ጌታቸው ረዳ የተቋቋመው ስምረት የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን ላቀረበው ጥያቄ ግንቦት 18 ቀን 2017  ከምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ እንደተሰጠው ይታወሳል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates