መካከለኛ ምስራቅ
የእስራኤል እና ኢራን ጦርነት 6ኛ ቀኑን ይዟል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/10/2017፡ ሁለቱም ወገኖች እርስ በርስ መታኮሳቸውን ቀጥለዋል። እስራኤል ትናንት ሌሊት በቴህራን የሚገኘውን የዩራኒየም ማብላያ እና ጦር መሣርያ ማምረቻ መምታቷን ገልጻለች።
ኢራንም ማዕከላዊና ሰሜናዊ እስራኤልን በሚሳኤል ስትደበድብ ነበር። በዚህም ሰዎች ስለመጎዳታቸው ተሰምቷል።
ሁለቱ አገራት አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ የሚሳዔል እና የአየር ጥቃት እየፈጸሙ ሲሆን ነዋሪዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ ቅድመ ማስጠንቀቂያ በተደጋጋሚ እየሰጡ ነው።
አሜሪካ ከእስራኤል ጋር ለማበር እያጤነች መሆኑ ተሰምቷል። አሜሪካ ከእስራኤል ጎን ተሰልፋ በኢራን ላይ በሚካሄደው ጥቃት የምትሳተፍ ከሆነ ግጭቱን ወደ አልተጠበቀ አቅጣጫ ሊወስደው ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።
የአሜሪካው መሪ ዶናልድ ትራምፕ ” ትዕግሥታችን እያለቀ ነው ” ሲሉ አጠንቅቀው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ኢራን እጅ መስጠት እንዳለባት ተናግረዋል።