ማህበራዊኢትዮጵያ

በትግራይ መቐለ ከተማ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/10/2017፡ ለሶስት ተከታታይ ቀንና ለሊት ሊካሄድ የታቀደውን ” ለአምስተኛው ክረምት በሻራ ይበቃል” ሰላማዊ ሰልፍ በመቀሌ ከተማ ሮማናት አደባባይ ተጀምሯል።

የትግራይ ህዝብ ጥፋት ይቁም! , አስከሬን መቁጠር ይቁም! ፣ ህዝባችንን ከወራሪ ሐይሎች ነፃ ይውጡ! ፣ የትግራይ ክልል ግዛታዊ አንድነት ይከበር! የተፈናቃዮች ድምጽ ይሰማ! የሚሉት መፈክሮች በመያዝ ተፈናቃዮቹ አደባባይ ወጥቷል።

የሰልፉ ዋና አላማ ለአምስተኛው ክረምት በተለያዩ የስደተኞች መጠለያ ካምፖች ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ተጎጂዎችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ቤታቸው መመለስ ነው። የሰልፉ አዘጋጅ ፅላል የተሰኘው የምዕራብ ትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ እንደገለፀው ሰልፉ በፕሪቶሪያ ስምምነት ፈራሚዎች ላይ በተለይም በፌደራል መንግስት እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ላይ ጫና ለመፍጠር ነው።

በሮማናት አደባባይ በተካሄደው “ይበቃል” ሰላማዊ ሰልፍ የተፈናቀሉ ዜጎች፣ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች እና የሲቪል ማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል። ሰላማዊ ሰልፉ ከሰኔ 11 እስከ ሰኔ 13/2017 ዓ/ም ድረስ የሚካሄድ ሲሆን በስዊዘርላንድ ዋና ከተማ እና የተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት በጄኔቫም ይካሄዳል ተብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates