ፖለቲካ

ትራምፕ የቡድን 7 ጉባዔ ሳይጠናቀቅ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተነገረ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/10/2017፡ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረውን ውጥረት ለመከታተል ሲሉ፤ የቡድን 7 (G7) ጉባዔ ሳይጠናቀቅ  ወደሀገራቸው መመለሳቸው ታውቋል።

በካናዳ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድን 7 ጉባዔ አጭር ቆይታ ያደረጉት ትራምፕ “በተቻለኝ ፍጥነት መመለስ አለብኝ” ሲሉ ለጋዜጠኞች መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። “በግልጽ በሚታወቁ ምክንያቶች ቀድሜ መመለስ አለብኝ” ሲሉ የተደመጡት ትራምፕ፤ በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረውን ውጥረት ለመከታተል እና ከኢራን ጋር የሚካሄደውን ድርድር ዳግም ለማስጀመር ፍላጎት እንዳላቸው ሲኤንኤን ዘግቧል።

ትራምፕ ካናናስኪስ በተሰኘችው የካናዳ የመዝናኛ ከተማ ከመሪዎች ጋር ከተወያዩ በኋላ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ “ኢራን በመሠረቱ ስምምነት ለማድረግ ወደ ድርድር ጠረጴዛ የቀረበች ይመስለኛል፤ እኔም ከዚህ እንደወጣሁ አንድ ነገር እናደርጋለን” ብለዋል። ትራምፕ በተመሳሳይ እ.አ.አ. በ2018 የቡድን 7 ጉባዔን ጥለው መውጣታቸው ይታወሳል።

የቡድን 7 አገራት መሪዎች በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን ውጥረት እንዲረግብና በውይይት እንዲፈታ ጥሪ አቅርቧል። ሆኖም ኢራን የኒኩሌር መሳሪያ እንዲኖራት እንደማይፈቅዱ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቋል።
ትራምፕ ሩስያ ከቡድን 8 አገራት መውጣቷ ስህተት ነበር ሲሉም ተደምጧል።
“G7 ቀድሞ G8 ነበር ባራክ ኦባማ እና ትሩዶ የተባለ ሰው ሩሲያ መግባት የለባትም ብሎ አሰወጧት፤ ያ ስህተት ነበር እላለሁ፤ ምክንያቱም ሩሲያ ብትገባ አሁን ጦርነት አይኖርም ብዬ አስባለሁ” ሲሉም ተደምጧል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates