አፍሪካፖለቲካ

ኤርትራ የኮንሰንትሬሽን ማእከል ሆናለች ሲል የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት አመለከተ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/10/2017፡ በኤርትራ የሰብአዊ መብት ሁኔታ ልዩ ራፖርተር መሀመድ አብደልሰላም ባቢከር “የኤርትራ ህዝብ መብት የመደራደር ወይም የፖለቲካ ምቾት ጉዳይ አይደለም” ብለዋል። ልዩ ራፖርተሩ ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት
“በኤርትራ ያለው ሁኔታ የማይለዋወጥ አይደለም። እየተባባሰ ነው ያለው፤ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ስርዓታዊ ናቸው። በዚህም የተጠያቂነት ጉዳይ አስቸኳይ መሆን አለበት” ብለዋል።
“ያለ ፍርድ ለአስርት ዓመታት የታሰሩት ዜጎች የት እንዳሉ ሰምተን አናቅም” ያሉት ባቢከር የኤርትራ ወጣቶች በፍርሃትና በስቃይ ህይወታቸው አደጋ ላይ እንደሚጥሉ ለፀጥታው ምክር ቤት አስረድቷል። የኤርትራ መንግስት በተለያዩ ጊዝያት በሰብአዊ መብት ጥሰቶች ቢከሰስም በአለም አቀፉ ማህበረሰብ እስካሁን የተወሰደ እርምጃ የለም።
ይሁን እንጂ የኤርትራ መንግስት ሪፖርቱን ፖለቲካዊ ወንጀላ ሲል አጣጥሎታል። የስርዓቱ ተወካይ ሃብቶም ዘርአይ በመድረኩ ባስተላለፉት መልእክት” በጥላቻ እና በሽረባዎች የሚመሩ ፖለቲካዊ ተነሳሽነት ያላቸው ሪፖርቶች አንቀበልም” ብሏል።


“የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 80 ዓመት ቢሞላውም፣ ይህ ምክር ቤት ሉአላዊነትን የሚጥሱ፣ እውነታዎችን ችላ የሚሉ እና የአንዳንድ ኃያላን አባል ሀገራትን መብቶች ለማስተናገድ ተጨባጭነትን የሚጥሱ ትዕዛዞችን መቀበል የለበትም” ሲሉም ተደምጧል።
ከዚህ በተጨማሪ የኤርትራ መንግስት ድርጅቱ የያዘውን የኤርትራ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ምርመራ እንድያቋርጥ ጥሪ አቅርቧል።
“ኤርትራ ይህ ስልጣን እንዲቋረጥ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ አቅርቧል። ስለሆነም ሁሉም የዚህ ምክር ቤት አባላት በኤርትራ ላይ የተሰጠው ልዩ የራፖርተር ስልጣን ከህጋዊ መሰረቷ የራቀ፣ ተአማኒ የሆኑ ግኝቶችን ያላቀረበ እና ለሰብአዊ መብት ጥሰት የሚዳርገው ተልዕኮ እንዲያቆም እንጠይቃለን” ብለዋል ተወካዩ።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates