
ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/10/2017፡ በምእራብ ትግራይ የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ለስድስት አመታት ያህል ከትምህርት ገበታ ርቀው እንደሚገኙ ተገለፀ።
በማይ ፀብሪ ፣ ፀለምቲ እና ዲማ ወረዳዎች የትምህርት አገልግሎት ለስድስት ዓመታት ያህል በመቋረጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ህፃናት ከትምህርት ገበታቸው እንደቀሩ የኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል አስታውቋል።
እንደ አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ግምት ከሆነ እ.አ.አ. በ2024 አጋማሽ ከ40,000 እስከ 85,000 የሚደርሱ በአገር ውስጥ ተፈናቅለው በእነዚህ አካባቢዎች ይኖራሉ። የኖርዎይ ስደተኞች ካውንስል መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ ከጦርነቱ በፊት በሦስቱ ወረዳዎች ውስጥ ያሉ ህጻናት በ 61 የመጀመሪያ ደረጃ እና ስድስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይማሩ ነበር። አሁን ከ41,000 በላይ ህጻናትን ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደሆኑ መረጃው ያሳያል።
ትላንት የአፍሪካ ህፃናት ቀን በተከበረበት ወቅት የትግራይ ክልል የማህበራዊ ጉዳይና የመልሶ መቋቋም ቢሮ ሐላፊ ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ እንዳሉት በአሁን ወቅት በትግራይ 49 በመቶ ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው።