ፖለቲካ

ኢራን ቴሌቪዥን ጣቢያ ተመታ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/10/2017፡ የኢራን ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የቀጥታ ስርጭት ላይ እያለ በሚሳኤል ተመታ፡፡

የእስራኤል ሀይሎች ትላንት በፈፀሙት ጥቃት የኢስላሚክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኢራን ኒውስ ኔትወርክ(ኢሪን) ዋና ፅህፈት ቤት ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ተገልጿል፡፡ በጥቃቱ ክንያት በቀጥታ ስርጭት ላይ የነበረው የቴሌቪዥን ጣቢያው ተቋርጧል፡፡

ይህ ጥቃት የደረሰው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኢል ካትዝ “የኢራን የፕሮፖጋንዳና አፈቀላጤ መሳሪያዎች እንዲጠፉ ይደረጋሉ” ካሉ ከትንሽ ሰዓታት በኋላ ነው፡፡ የኢራን ሚዲያዎች እንደዘገቡት ይህ ጥቃት የተፈፀመው ዜና አቅራቢዋ በእስራኤል ላይ ትችት እያቀረበች በነበረችበት ወቅት ነው፡፡
የቴሌቪዥን ስቱዲዮው በጥቃቱ ተመቶ ግድግዳው ሲፈራርስ በቀጥታ ስርጭት የታየ ሲሆን አቅራቢዋም ወዲያውኑ ከመቀመጫዋ ተነስታ ከአካባቢው ወጥታ ስትሄድ ታይታለች፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates