
ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/10/2017፡ የትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያን ጨምሮ በ36 ሀገራት ተጨማሪ የጉዞ እገዳ ሊያደርግ መሆኑን ተገለፀ።
ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወሻ እንደሚያሳየው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በትራምፕ አስተዳደር የታወጀውን የጉዞ እገዳ ጉልህ በሆነ መልኩ ወደ ተጨማሪ የ36 ሀገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ለማገድ እያሰበች ነው።
ከአዲሱ የቪዛ እገዳ ወይም ሌሎች እገዳዎች መካከል 25 የአፍሪካ ሀገራት፣ እንደ ግብፅ እና ጅቡቲ ያሉ ጉልህ የአሜሪካ አጋሮች፣ እንዲሁም በካሪቢያን ፣ መካ ከለኛው እስያ እና በርካታ የፓሲፊክ ደሴት ሀገራት ያሉ ሀገራት ይገኙበታል።
በውጭ ጉዳይ ማርኮ ሩብዮ ተፅፎ በአገሪቱ ወደሚገኙ ዲፕሎማቶች ቅዳሜ ዕለት የተላከውን ማስታወሻ እንደሚያመለክተው አገራቱ በውጭ ጉዳይ የተዘረዘሩት መነሻ ሓሳቦች እንድያማሉ 60 ቀን ተሰጥቷቸዋል።
በአሜሪካ የጉዞ እገዳ ከተጣለባቸው 36 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች። ሰነዱ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በወጣው የጉዞ እገዳ ላይ በመመስረት የትራምፕ አስተዳደር የስደተኞች ፖሊሲ ጉልህ መስፋፋት አካል ነው ተብሏል። በቀረበው ዝርዝር ውስጥ 25 የአፍሪካ ሀገራት ማለትም ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ናይጄሪያ፣ ጅቡቲ እና ጋና እንዲሁም የካሪቢያን ፣ የመካከለኛው እስያ እና የፓሲፊክ ውቅያኖስ አገራት ያጠቃልላል። በማስታወሻው መሰረት፣ አንዳንድ ሀገራት “ታማኝ የመታወቂያ ሰነዶችን የማምረት ብቃት ያለው ወይም የትብብር ማእከላዊ መንግስት ስልጣን የላቸውም” ሌሎች ደግሞ “በተንሰራፋ የመንግስት ማጭበርበር” ወይም በዩኤስ ውስጥ “ቪዛቸውን ከልክ በላይ የቆዩ” ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ጠቅሷል። ለማካተት ሌሎች ምክንያቶች የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖር የዜግነት ሽያጭ እና ከተወሰኑ አገሮች የመጡ ግለሰቦች “በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ፀረ-ሴሚቲክ እና ፀረ-አሜሪካዊ ተግባር” ላይ የተሳተፉ ውንጀላዎች ያካትታል።
ባለፈው ግንቦት #ኤርትራ፣ #ሱዳን እና #ሶማሊያን ጨምሮ ሰባት የአፍሪካ አገራት ባሉባቸው 12 አገራት ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአገራቸውን እና የሕዝባቸውን ደኅንነት ለመጠበቅ በሚል ትዕዛዝ ፈርመው ተግባራዊ መሆኑ ይታወሳል።
አሜሪካ የአገራት እግድ ስታኑር ቻይና በአንፃሩ 51 የአፍሪካ አገሮች ከቀረፅ ነፃ የንግድ ትስስር ለመፍጠር መወሰኗ መረጃዎች ያሳያሉ።