
ኢትዮ ሞኒተር: 05/10/2017: የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎች (RSF) ትላንት እንደገለፁት ተዋጊዎቻቸው ከግብፅ እና ከሊቢያ ጋር በሚያዋስኑት ድንበር ላይ የሚገኘውን ስትራቴጂካዊ ቀጠና ተቆጣጥሯል። የሱዳን ጦር ሃይል በበኩሉ ከአካባቢው መውጣቱን አስታውቋል።
የሰራዊቱ ቃል አቀባይ ናቢል አብደላህ በሰጡት መግለጫ “የእኛ ሃይሎች ጥቃትን ለመመከት ባደረገው የመከላከያ ዝግጅት አካል ዛሬ በሱዳን፣ በግብፅ እና በሊቢያ መካከል ያለውን ድንበር የሚመለከተውን የሶስት ማዕዘን አካባቢ ለቀው ወጥተዋል ብለዋል። RSF እንዳስታወቀው ግን “ስትራቴጂካዊውን የሶስት ማዕዘን አካባቢ ነፃ አውጥተናል” ሲል የመንገስት ሠራዊት ኃይሎች “ከባድ ኪሳራ ከደረሰባቸው በኋላ ወደ ደቡብ አቅጣጫ አፈግፍጓል” ብሏል።
ይህ ሁኔታ የተከሰተው የሱዳን ሰራዊት የምስራቅ ሊቢያ አዛዥ የሆኑት ካሊፋ ሃፍታር ከRSF ጎን ለጎን ድንበር ዘለል ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ከከሰሰ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። “በሱዳን ላይ ግልጽ የሆነ ወረራ ተፈፅሟል ያለው የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ጥቃቱን እንደደገፈች በመግለጽ ድርጊቱን “አደገኛ መባባስ” እና “የአለም አቀፍ ህግን አጉልቶ የጣሰ” ሲል ገልፆታል።