አፍሪካፖለቲካ

የኡጋንዳ መንግስት ለኤርትራውያን የፖለቲካ ጥገኝነት ከለከለ።

ኢትዮ ሞኒተር: 04/10/2017: የአፍሪካ ኢንተለጀንስ ድረ-ገጽ እንደዘገበው የኡጋንዳ መንግስት እገዳውን የጣለው ህገ-ወጥ የሰዎች እና የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ነው።

ኤርትራዊያን ወደ ዩጋንዳ እንዳይገቡ እገዳው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ የጠራ መረጃ የለም። በኡጋንዳ በሻአቢያ መንግስት ጭቆና ምክንያት ብዙ ኤርትራውያን ይኖራሉ። በዋና ከተማዋ ካምፓላ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ኑሮአቸውን እየመሩ ነው።

የኡጋንዳ መንግስት በአዲስ ኤርትራዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ የጣለው እገዳ በኤርትራውያን ዘንድ ስጋት ፈጥሯል።

በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኤርትራዊያንን ጨምሮ በ12 ሀገራት ዜጎች ላይ የጉዞ እገዳ ጥለው ባለፈው ሰኞ ተግባራዊ መሆኑን ይታወሳል።

ትራምፕ ባለፈው ሳምንት የ12 ሀገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚያግድ አዲስ ህግ ቢፈራረሙም በኤርትራ መንግስት አፈ ቀላጤዎች እንደሆኑ የሚነገርላቸው ድህረ ገፅ ሚድያዎች እገዳው ተገቢ እንደሆነ  ዘግቧል። ኤርትራ ፕሬስ የተባለ በየነ መረብ እንደዘገበው እገዳወሰ ኤርትራዊያን አገራቸው ትቶ እንዳይወጡ የሚያደርግ ስለሆነ ሊወገዝ አይገባምጰይላል።
የኤርትራ ወጣቶች ከአገራቸው የሚሰደዱበት ምክንያት ለ30 ዓመታት የዘለቀ ወታደራዊ አገልግሎት፣ ስራ አጥነትና የነፃነት እጦት አንገሽግሻቸው እንደሆነ ይነገራል።
በአምባገነን መንግስታት፣ በጦርነት እና በድርቅ ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ባህር እና በረሃ አቋርጦ እንዲሰደዱ በተገደዱበት በዚህ ወቅት; እንደ አሜሪካ እና ኡጋንዳ ያሉ ሀገራት ደግሞ በስደተኞች ላይ ገደብ ጥሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates