
ኢትዮ ሞኒተር፡ 03/10/17፡ የኢትዮጵያ እና ኢትሃድ አየር መንገዶች በመጋቢት ወር በአዲስ_አበባ የተፈራረሙትን ‘የኮድ ሼር ስምምነት’ ተግባራዊ ማድረጋቸውን አስታውቋል። ይህም በአፍሪካ እና በእስያ፣ በ አውስትራሊያ እና በመካከለኛው ምስራቅ መካከል ያለውን ትስስር የሚያጠናክር ነው ተብሏል።
የኮድ ሼር’ ስምምነቱ ተግባራዊ መሆን፤ በሁለቱ አየር መንገዶች መካከል በመጋቢት ወር የተፈረመውን የጋራ የቢዝነስ ስምምነት ተግባራዊ የሚያደርግ የመጀመሪያው እርምጃ መሆኑም ተገልጿል። ስምምነቱ፤ በሁለቱም በኩል ላሉ ለተጓዦች የተሻል ዓለም አቀፍ የጉዞ ዕድሎችን ይከፍታል ተብሏል።
የኮድ ሼር አገልግሎት፤ ተጓዦች ሁለቱ አየር መንገዶች የሚደረጉትን የተላያዩ በረራዎችን መጠቀም የሚችሉበት አማራጭ የሚያቀርብ ስርዓት ነው። በተጨማሪም ሻንጣዎችን ወደ መጨረሻ መድረሻቸው በቀላሉ በማስተላለፍ ጉዞን የሚያቃልል መሆኑንም ታይምስ ኦፍ ኤሮስፔስ ዘግቧል።
በዚህ አጋርነት መሰረት፤ የኢትሃድ አየር መንገድ ተጓዦች፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ሰፊ የአፍሪካ ሀገራት በረራ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ። በዚህም በአዲስ አበባ በኩል ኢንቴቤ፣ ኪንሻሳ፣ ኪጋሊ፣ ሉሳካ፣ ሃረሬ እና ቪክቶሪያ_ፎልስን ጨምሮ በ33 ሀገሮች ወደሚገኙ 55 መዳረሻዎች መጓዝ ይችላሉ።