ማህበራዊአፍሪካኢትዮጵያ

ስዊድን ለዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ፕሮግራም ለማህበራዊ አገልግሎት የሚውል 7.8 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች

ኢትዮ ሞኒተር

አዲስ አበባ 26/09/5017:ስዊድን በኢትዮጵያ  ማኅበራዊ ጥበቃ፣ በኑሮ ማሻሻያ እንዲሁም በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርሱ ጫናዎችን የመቋቋም አቅም ለማጠናከር ለተዘጋጀ አዲስ ፕሮግራም  7.8 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለዩኒሴፍ  እንደምታደርግ አስታወቀች።

የድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር የሆኑት ሀንስ ሄንሪክ ላንድኲስት እና በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ዶ/ር አቡበከር ካምፖ ትናንት ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል።

“ጠንካራ የመቋቋም አቅምና ኑሮን ማሻሻል፤ ማኅበራዊ ጥበቃ ለሴቶችና ሕፃናት” በሚል ርዕስ የቀረበው ይህ ፕሮግራም፣ 34,650 የሚገመቱ አባወራዎች ውስጥ የሚገኙ 173,250 ግለሰቦችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።

በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር የሆኑት ሀንስ ሄንሪክ ላንድኲስ ፕሮግራሙ ተጋላጭ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ሴቶችና ሕፃናትን እንደሚደግፍ ገልጸው በተጨማሪ ደግሞ ኢትዮጵያ ለሕዝቧ ኃላፊነትን ለመውሰድ የምታደርገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates