
ኢትዮ ሞኒተር
አዲስ አበባ 26/09/5017 : የማይክሮሶፍት መስራች ቢልጌትስ፤ በቀጣዮቹ 20 ዓመታት ካላቸው ሀብት ውስጥ አብዛኛውን በአፍሪካ የጤና እና ትምህርት አገልግሎቶችን ለማሻሻል እንደሚያውሉት ተናግሯል። የ69 ዓመቱ ባለጸጋ፤”በጤና እና ትምህርት የሰው ልጅን በማውጣት፤ አፍሪካ ውስጥ እያንዳንዱ ሀገር በብልጽግና ጎዳና ላይ መሆን አለበት” ብሏል።
ቢል ጌትስ ባለፈው ሳምንት እሁድ ግንቦት 24/2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በብሔራዊ ቤተመንግሥት በተካሄደ ሥነሥርዓት የሀገሪቱን ታላቅ የክብር ኒሻን ሽልማት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተሸልሟል። ዐቢይ፤ ይህንን ሽልማት ለጌትስ ያበረከቱት በባለሀብቱ የመሰረተው ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ “ባለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ላበረከታቸው አሻጋሪ ሥራዎች እና ታላላቅ ዘመን ተሻጋሪ በጎ ተፅዕኖዎችን” እውቅና ለመስጠት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ቢል ጌትስ በአዲስ አበባ ከተማ ባደረጉት ንግግር አፍሪካውያን ወጣት ፈጣሪዎች ሰው ሰራሽ አስተውህሎትን በምን አይነት መንገድ በመጠቀም በአህጉራቸው የጤና አገልግሎትን ማሻሻል እንደሚችሉ እንዲያስቡ አሳገንዝቧል። ቤልጌትስ ከ20 ዓመት በኋላ 200 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ከሚጠበቀው ሀብታቸው ውስጥ 99 በመቶውን ለመስጠት ማቀዳቸው ያስታወቁት ባለፈው ወር ነበር። የባለሀብቱ ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በ2045 ስራውን ያጠናቅቃል። በአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት በተዘጋጀው ስነ ስርዓት ላይ “በቀጣዮቹ 20 ዓመታት ውስጥ ያለኝን ሀብት እንደሚከፋፈል በቅርቡ ቃል ገብቻለሁ። አብዛኛው ገንዘብ አፍሪካ ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን እንድትፈቱ ለማገዝ ይውላል” በማለት ተናግሯል።