አፍሪካየአየር ንብረት አካባቢ

ግብፅ በበረሀ ላይ አዲስ ከተማ ልትገነባ መሆኑን አስታወቀች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር

አዲስ አበባ 26/09/5017 : የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ ይፋ ያደረጉት ይህ አዲስ ፕሮጀክት ግብፅ ከአባይ ወንዝ ከሚደርሳት ውሀ ላይ 7 በመቶ የሚጠቀም መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንደሚኒስትሩ ገለፃ ይህ አዲስ ከተማ ‹‹ጂሪያን›› ተብሎ የሚጠራ ነው፡፡ ከካይሮ በስተምእራብ የሚገነባው ይህ አዲስ ከተማ የአባይ ውሀን በመጠቀም መጠነ ሰፊ እርሻ እንደሚኖረው የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አላማውም አገሪቱን ስንዴን በመሳሰሉ ወሳኝ የግብርና ምርቶች ራሷን እንድትችል ማድረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የጂሪያን ከተማ ግንባታ ፕሮጀክት እቅድ የወጣው እ.ኤ.አ በ2021 እንደነበር ገልፀውም ከአገሪቱ ከምታስፈፅማቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች አንዱ በመሆን አሁን ወደትግራ መገባቱን አስታውቀዋል፡፡ ‹‹የጂሪያን ፕሮጀክት በከተማ ልማት ላይ አብዮት የሚፈጥር ነው›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተማው አራት ወይንም አምስት ወረዳዎችን የሚሸፍን እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡

እንዲሁም እስከ ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ የሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ገልፀዋል፡፡ የፕሮጀክቱ ሀላፊዎች እንደተናገሩት በጂሪያን ከተማ በየቀኑ ወደአስር ሚሊዮን ኪዩብ ሜትር የአባይ ውሀ እንዲፈስ በማድረግ እስከ ስድስት ሚሊዮን ካሬ ሜትር መሬትን በመስኖ ለማልማት ታስቧል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates