
ኢትዮ ሞኒተር
አዲስ አበባ 26/09/5017: “ድምፅ ነፃነት ትግራይ” በእንግሊዘኛ ምህፃረ ቃሉ VIT የተባለው የእንቅስቃሴ አደረጃጀት በትላንትናው ዕለት መመስረቱ ተገልጿል።
ይህ በተጋሩ ድያስፖራ የተጀመረው እንቅስቃሴ
ትግራይን ሙሉ ነፃነት ፍትህ፣ ክብር እና ራስን በራስ የማስተዳደር ዘመን ለማምጣት ያለመ ነው ተብሏል። እንደ ፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን ዓላማው ተጋሩን በአንድ ዓላማ ዙሪያ አንድ ለማድረግ ነው፤ ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብታቸውን ለማስመለስ እንደሆነ የእንቅስቃሴው መስራቶች አስታውቋል።፡
መስራቶቹ በሰጡት መግለጫ “እኛ ለነጻነት እየለመንን አንኖርም” “በመከራ የተገኘ፣ በደም የታነፀ እና ለመጥፋት ፈቃደኛ ያልሆነ የትግራይ ህዝብን የመብት ፍላጎት እየጠየቅን ነው።” ብሏል።
የንቅናቄው መጀመር ከዓመታት ጦርነት፣ ረሃብ እና የፖለቲካ መገለል በኋላ የመጣ ነው እንደሆነም ተገልጿል።
መግለጫው ከቅርብ አመታት ወዲህ በተጋሩ ላይ የደረሰ ያለውን ግፍ ወደር የማይገኝለት ነው ሲል ይገልፃል።
“ትግራይ ወደ ግድያ ሜዳነት ተቀየረች፣ ሲቪሎች በየቤታቸው ታረዱ፣ ሴቶች ሆን ተብሎ ተደፈሩ፣ መላው ማህበረሰብ በረሃብ ረገፈ፣ የባህል ቅርሶቻችን በቦምብ ተቃጥለዋል” በማለት የሁለት ዓመቱ አውዳሚ ጦርነትን አስታውሷል።
ከሰላም ስምምነቱም በኃላ ግዛቱን ተወሮ ወደ ቅያው እንዳይመለስ ተከልክሎ እስከመቼ እያለቀ ይኖራል በማለት ይጠይቃል።
የትግራይ ህዝብ በኢ/ያ መንግስት እየተገፋ ነው የሚለው ድምፅ ነፃነት ትግራይ በዚህም የወደፊት ቤቱን የመገንባት ጉዞ አሁን መጀመር እንዳለበት አስገንዝቧል።