አፍሪካ

የሱዳኑ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይል መሪ ጄነራል መሐመድ ዳጋሎ ግብፅን ከሰሱ።

የሱዳኑ ሄሜቲ በኤል ኦቤይድ ጥቃትን እንደሚፈፅሙም ዝቷል።

ኢትዮ ሞኒተር

አዲስ አበባ 26/09/5017: የፈጣን ድጋፍ ሃይሎች (RSF) አዛዥ መሀመድ ሃምዳን ዳግሎ ሄሜቲ  በሰሜን ኮርዶፋን ግዛት እና በሰሜናዊ ግዛት በሚገኘው ኤል ኦቤይድ ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ እንደሚችሉ በመግለጽ ግብፅ የ RSF ቦታዎችን እያጠቃች ነው  በማለት ከሷል። ግብፅ የሱዳን ሰራዊትን ትደግፋለች በማለትም ውንጅሏል። ባለፈው ሳምንት አል-ካዊን እና አል-ደብይባትን መልሰው የያዙትን የዳርፉር እና የኮርዶፋን ተዋጊዎች ካሰባሰቡ በኋላ የRSF ሃይሎች በኤል ኦበይድ ዙሪያ ከሶስት አቅጣጫዎች ማለትም አል-ካዊ፣ሀምርት አል-ሼክ እና አል-ሃማዲ ለማጥቃት መዘጋጀታቸው እየተገለፀ ነው። ” ኃይላችን በማንኛውም ጊዜ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ነው” ሲሉ ሄሜቲ በ RSF የቴሌግራም መድረክ ላይ ባቀረቡት ንግግር ላይ ተሰምቷል። የኤል ኦበይድ ነዋሪዎች ቤት እንዲቆዩ፣ ሱቆችን እንዲዘጉ እና ከወታደራዊ ቦታዎችን እንዲርቁም አሳስቧል ጄነራል መሐመድ ዳጋሎ።  ሄሜቲ በሰሜናዊ ግዛት በሜሮዌ፣ አድ-ዳባ እና ዶንጎላ ከተሞች ከኢላማዎች ዝርዝር እንደሆኑ በመግለጽ ለእስላማዊ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አሊ ካርቲ እና መሪዎቹ አህመድ ሃሩን እና ኦሳማ አብደላህ ታማኝ የሆነ ማንኛውም ሰው “ለኛ ህጋዊ ኢላማ” መሆኑን እንገልፃለን ብሏል። ሄሜቲ በደቡብ ኮርዶፋን እና በምዕራብ ኮርዶፋን የሚገኘውን አል-ካዊን መልሶ መያዛቸውን አስታውቋል።
ይሁን እንጂ የሱዳን ሰራዊት አሁንም የበላይነቱ እንደያዘ ይገልፃል።

ይህ በእንዲህ እያለ በሰሜን ዳርፉር እየተባባሰ የመጣውን ግጭት ሸሽተው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ስደተኞች ከሚያዝያ ወር ጀምሮ ምስራቃዊ ቻድ መድረሳቸውን የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ገልፃል። ከፍተኛ የእርዳታ እጥረት በማጋጠሙ የከፋ ሰብአዊ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችልም  ድንበር የለሽ ዶክተሮች ትላንትና አስጠንቅቋል።

ከሚያዝያ 2025 ጀምሮ ወደ 70,000 የሚጠጉ አዳዲስ ስደተኞች ወደ ቻድ ገብተዋል፣ ይህም ከሁለት አመት በፊት ግጭት ከጀመረ ወዲህ በአጠቃላይ በቻድ የተጠለሉ ሱዳናውያን ቁጥር ከ800,000 በላይ አድርሶታል። ቻድ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን የምታስተናግድ አገረሰ መሆኗ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates