ፖለቲካ

የቀድሞው የመከላከያ ሠራዊት የምድር ኃይል ዋና አዛዥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 02/07/2018፡- ሌተናንት ጄነራል አስራት ደኔሮ የመከላከያ የምድር ኃይል ዋና አዛዥ እንዲሁም የሠራዊቱ መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ በመሆን ያገለገሉ ናቸው፡፡

ላለፉት ሰባት ዓመታት ገደማ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ጌቱ አርጋው እና ሁለት ምክትል ኮሚሽነሮች ከኃላፊነት እንደተነሱ ተሰምተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተነሱት አመራሮች ምትክ የቀድሞው የመከላከያ የምድር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናንት ጄነራል አስራት ደኔሮን እና ሁለት ምክትል ኮሚሽነሮችን ሾመዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መረጃ ሌተናንት ጄነራል አስራት ደኔሮን የአዲስ አበባ ፖሊስን በኮሚሽነርነት እንዲመሩ መሾማቸውን ገልጿል።

አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙ ሌተናንት ጄነራል አስራት፤ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ረጅም ጊዜ የቆዩ ወታደራዊ አዛዥ ናቸው።

ሌተናንት ጄነራል አስራት፤ ከዚህ ቀደም የመከላከያ ሠራዊት የምድር ኃይል ዋና አዛዥ እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ በመሆንም አገልግለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምክትል ኮሚሽነት የሾሟቸው ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ እና እርዚቅ ኢሳን ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates