አፍሪካ

የተባበሩት መንግስታት የደቡብ ሱዳን ተልእኮ በአኮቦ የሚገኙ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሲቪል ጥበቃን እንዲያከብሩ ጥሪ አቀረበ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 01/07/2018፡- የደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት ተልዕኮ እ.አ.አ መጋቢት 6 ቀን በደቡብ ሱዳን የህዝብ መከላከያ ሰራዊት በአኮቦ ከተማ እና በዙሪያዋ ባሉ መንደሮች ውስጥ ያሉ ሲቪሎች ከታቀደው ወታደራዊ እንቅስቃሴ በፊት ወደ ሌላ እንዲሰፍሩ መመሪያ ከሰጠ በኋላ ከሀገር አቀፍ፣ ከክልል እና ከአካባቢ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ መሆኑ አስተውቀዋል።

በተመሳሳይ ሪፖርት የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ እና የሰብአዊ እርዳታ አጋሮች በ72 ሰዓታት ውስጥ አኮቦን ለቀው እንዲወጡ የአገሪቱ ሰራዊት ማዘዙ ይታወሳል።

“በአኮቦ እና አካባቢው የሚደረግ ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሲቪሎችን ደህንነት እና ፀጥታ በእጅጉ አደጋ ላይ ይጥላል” ሲሉ የተልእኮው ኃላፊ አኒታ ኪኪ ግቤሆ ተናግረዋል።

“ስለዚህ፣ ማህበረሰቦችን ለመጠበቅ ሁሉንም እርምጃ እንደሚወስዱ በሁሉም ወገኖች በተሰጡት ማረጋገጫዎች ላይ እንተማመናለን” ያሉ ሲሆን ተልእኮው የሰላም አስከባሪ ሃይሎቹ በአኮቦ እንደሚቆዩ እና ለሲቪሎች ጥበቃ እንደሚሰጡ አረጋግጧል።

የደቡብ ሱዳን ሰራዊት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘው የአኮቦ ግዛት ላይ በታጣቂዎች ወታደራዊ ዘመቻ እንደሚጀምር ማስታወቁን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱ እንደሆኑ ተዘግበዋል፡፡

የአኮቦ አከባቢ የምክትል ፕሬዝዳንቱ ሬክ ማቻር ደጋፊ በሆኑት ታጣቂዎች ስር የሚገኝ ቦታ ሲሆን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ሬክ ማቻርን በማሰር ኣሁን በታጣቂው ላይ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

ይህ ክስተት አገሪቱ ወደለየለት የአርስበርስ ጦርነት እንዳትገባ ከፍተኛ ስጋት ተፈጥረዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates