የተለያዩ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን በወንጀል ከሰሰ፡፡

ኢትዮ ሚኒተር፡ 27/04/2018፡- ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) ሴቶችን በጅምላ በመድፈርና የማሰቃየት ወንጀሎችን ጨምሮ በበርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከሰሰ፡፡

ሰብዓዊ ተቋሙ “የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በታጣቂው የተፈጸሙ ጾታዊ ጥቃት፣ ከፍርድ ውጭ ግድያ እና የማሰቃየት ወንጀል ምርመራ ሊደረግባቸዉ ይገባልም” ብሏል፡፡

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተዋጊዎች ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ጾታዊ ጥቃት በመፈጸም ወንጀል ተጠያቂ ነው ብሏል፡፡

ተዋጊዎቹ የአስገድዶ መድፈር፣ “በቡድን መድፈር”፣ “ወሲባዊ ባርነት”፣ “ያለፍርድ ግድያ” እና የንጹሃን ሰላማዊ ዜጎች ንብረትን ማውደም የመሳሰሉ ወንጀሎችን ፈጽመዋል ሲልም ነው ሰብዓዊ ተቋሙ ባወጣው አዲስ ዘገባዉ የከሰሰው፡፡

ሰብዓዊ ድርጅቱ አክሎም በ2011 ዓ.ም ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተከፈተው የግጭት ሂደት ውስጥ የፈጸማቸው እነዚህ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ያስከተሉ ወንጀሎች “በጦር-ወንጀልነት”ሊፈረጁ የሚችሉም ናቸው ብሏል፡፡

እንደ ሰብዓዊ ድርጅቱ መግለጫ፤ ጥናቱ በተካሄደበት በአራቱ ዓመታት ዉስጥ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ቀሌም ወለጋ ዞን ሳዮ እና አንፍሎ ወረዳዎች “በኦነግ ተዋጊዎች” “የቡድን አስገተድዶ መድፈር፣ የወሲብ ባርነት እና በጅምላ መፈናቀልን” የመሳሰሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለተጋፈጡ ሴቶችና ልጃገረዶች የደረሰላቸው አካል አልነበረም ብለዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates