መካከለኛ ምስራቅ

ኢራን ግዙፍ ከመሬት በታች ያለ የዋሻ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አድርጋለች።

ኢትዮ ሚኒተር፡ 27/04/2018፡- በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ያለው ጦርነት በከረረበት በዚህ ወቅት ኢራን በርካታ ሚሳኤሎች እና የሻሄድ ድሮኖች የተከማቹበትን ግዙፍ ከመሬት በታች ያለ የዋሻ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አድርጋለች።

በመንግስት መገናኛ ብዙኃን የወጣው ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል ረጅም በሆኑ የኮንክሪት ዋሻዎች ውስጥ በረድፍ የተሰደሩ የሮኬት መተኮሻዎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ያሳያል።

ይህም ኢራን እነዚህን የጦር መሳሪያዎች በዝቅተኛ ወጪ እና በፍጥነት በብዛት የማምረት አቅም እንዳላት ” ጠላቶቼ ” ለምትላቸው ሀገራት ለማሳየት የተጠቀመችበት ስትራቴጂ ተደርጎ ተወስዷል።

ተንቀሳቃሽ ምስሉ፥ መጨረሻ የሌላቸው በሚመስሉ ዋሻዎች ውስጥ የተከማቹ የሻሄድ-136 ድሮኖች እና በከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ የተጫኑ ሚሳኤሎችን ያሳያል።

ኢራን በሀገር ውስጥ ድሮን ለመስራት የምታወጣው የማምረቻ ዋጋ ከ$20,000 እስከ $50,000 እንደሆነ ይነገራል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates