ፖለቲካ

“በጭራሽ ትግራይ ላይ የሚጀመር ጦርነት እንደሌለ ላረጋግጥ እወዳለሁ” ሲሉ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡

“ሻዕቢያ ዳግም ሕዝባችንን እንዲበድል እድል አንሰጥም ምናልባት ከሞከረ ደግሞ የመጨረሻ ሙከራው ነው የሚሆነው ብዬ ነው እኔ የማምነው" በማለትም አስተኝቅቀዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/06/2018፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ከፕሪቶሪያው አፈፃም እስከ ህወሐት እና ሻዕቢያ ያሉ ጉዳዮች ያነሱ ሲሆኑ የፌደራል ምንግስት ትግራይን ለመውረር ሰራዊት እያንቀሳቀሰ ነው ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ “በጭራሽ ትግራይ ላይ የሚጀመር ጦርነት እንደሌለ ላረጋግጥና ለመግለጽ እወዳለሁ” ሲሉ አስታውቀዋል።

ነገር ግን ህወሓት ከቃላት ፕሮፖጋንዳ አልፎ ወደ ትንኮሳ ከገባ ‘’ከም ቀደም ይመስለክን ውሕጅ ይወስደክን’’ ማለትም እንደ በፊቱ እንደ በፊቱ መስሎሽ ጎርፍ እንዳይወስድሽ የሚል የትግርኛ ተረት ተጠቅመዋል፡፡

ዐቢይ በማብራሪያቸው ህወሓትን “ከ 50 ዓመት በፊት በነበረ እሳቤ ቆሞ የቀረ” ቡድን ነው በማለት የተቹት ሲሆን ከሁለት ዓመት በላይ የተካሔደውን ጦርነት የቋጨውን የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዳይፈጸም ምክንያት የሆነውም ህወሓት ነው ሲሉ ከስሰዋል።

ስምምነቱን “ራሱ ከሕግ አፈንግጦ ለዳግም ጦርነት እንደምክንያት እያቀረበው ነው” በማለትም ህወሓት መአድን እየሸጠ የጦር መሳሪያ እየገዛ ነው ሲሉ ከስዋል።

የፌደራል መንግሥት የልማት በጀት እየላከ ቢሆንም ህወሓት ግን በጀቱን “ለታጣቂዎች ቀለብ እያዋለው ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ዐቢይ በትላንቱ ገለፃቸው ስለ ኤርትራ መንግሥትም ተናግረዋል። በትግራይ ጦርነት ወቅት የሻዕቢያ ሰራዊት ወደ ክልሉ ገብቶ ብዙ ውድመትና ጉዳት ማድረሱን አስታወሰዋል።

ከዚህ ኃይል ምንም ጥሩ ነገር ማግኘት የማይታሰብ ነው ያሉት ዐቢይ ሻዕቢያ “ዳግም ሕዝባችንን እንዲበድል እድል አንሰጥም ምናልባት ከሞከረ ደግሞ የመጨረሻ ሙከራው ነው የሚሆነው ብዬ ነው እኔ የማምነው” ብለዋል።

የሻዕቢያ ቡድን ከህወሓት በባሰ ልማት፣ የስልጣን ሽግግር እና ልጆጁ እና የልጅ ልጆቹ አያምንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ የኤርትራ ህዝብ ታታሪና የስራ ሰው ቢሆን አገሩን ጥሎ ወደ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ኡጋንዳ እየተሰደደ ነው ብለዋል፡፡

ሆኖም ኤርትራዊያን በኢትዮጵያ በሰላም እንዲኖሩ ብንፈልግም ሻዕቢያ ሰላዮች ቀላቅሎ እየላከ ጤናኛው ከበሽተኛው ለመለየት ተቸግረናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሻዕቢያ አሁንም አለሁ ለማለት ብቅ ጥለቅ እያለ ይገኛል ያሉ ሲሆኑ ለሻዕቢያ እንዲሁም ለኤርትራ ሰራዊት የማስተላልፈው መልእክት ‘’ቀንጠብጠብ ትብል ዳዋ ተምፅኦ ኣለዋ’’ ብለዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates