መካከለኛ ምስራቅ

ኳታር ለኢራን እየሰለሉ ነበር ያለቻቸውን 10 ሰዎች በቁጥጥር ሥር አዋለች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/06/2018፡- የኳታር የፀጥታ ኃይሎች ለኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ሲሰልሉ የነበሩ “ሁለት የስለላ ሕዋሶችን” ረቡዕ ዕለት በቁጥጥር ሥር ማዋሏን የአገሪቱ የመንግሥት የዜና ወኪል ዘገበ።

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ሰባቱ “የአገሪቱን ወሳኝ እና ወታደራዊ መሠረተ ልማቶች የተመለከተ መረጃ የመሰብሰብ የስለላ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው” እንደነበረ ዘገባው አመልክቷል።

በስለላ የተጠረጠሩት ቀሪዎቹ ሦስት ሰዎች ደግሞ “የድሮን አጠቃቀም ሥልጠና የወሰዱ” እንደሆኑ ተገልጿል።

የዜና ወኪሉ፤ “ተጠርጣሪዎቹ በተደረገባቸው ምርመራ ከኢራን አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አምነዋል፤ የስለላ እና የማዳከም ተልዕኮ ተሰጥቷቸው እንደነበር ተናግረዋል” በማለት ዘግቧል።

በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የተከፈተባት ኢራን በሰጠችው የአጸፋ ምላሽ ዒላማ ካደረገቻቸው የቀጣናው አገራት አንዷ ኳታር ነች። ኢራን በፈጸመችው ጥቃት የኳታር ዋነኛ የጋዝ ማምረቻ ተቋም ጉዳት እንደደረሰበት የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሁለት የኢራን ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ ሰባት ሚሳዔሎችን እና አምስት ድሮኖችንም መትቶ እንደጣለ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።

የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ትናንት በሰጡት መግለጫ “ሁሉም ቀይ መስመሮች ታልፈዋል” ብለው ነበር።

ጦርነቱ በተጀመረበት ቅዳሜ ዕለት ብቻ ኢራን 65 ሚሳዔሎችን እና 12 ድሮኖችን ወደ ኳታር ማስወንጨፏን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀው ነበር።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates