አፍሪካ

ሱማሊላንድ ለአሜሪካ የማእድንና የጦር ሰፈር ለመስጠት የሚያስችል መደራደሪያ አቀረበች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 16/06/2018፡- ራስ ገዝ የሆነችው ሱማሊላንድ የፕሬዝደንታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት ከድር ሁሴን ከኤኤፍፒ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ‹‹በማእድን ሀብታችን አሜሪካ በብቸኝነት እንድትጠቀም የሚያስችል መብት እንሰጣለን›› ብለዋል፡፡

ጨምረውም ‹‹አሜሪካ በግዛታችን ውስጥ ወታደራዊ ጦር ሰፈር እንድትመሰርት በራችን ክፍት ነው›› በማለት ገልፀዋል፡፡

ከ1991 አንስቶ ከሱማሊያ ተገንጥላ ራሷን እንደነፃ አገር የምትቆጥረው ሱማሊላንድ ከጥቂት ወራት በፊት ከእስራኤል የመጀመሪያውን አለም አቀፍ እውቅና ማግኘቷ የሚታወስ ነው፡፡

ይህንን እውቅና ማግኘቷን ተከትሎም እስራኤል በግዛቷ ወታደራዊ ጦር ሰፈር እንድትመሰርት የፈቀደች ሲሆን በዚህ ጉዳይ በቅርቡ ሁለቱ ስምምነት እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል፡፡

 

አሁን ደግሞ ለአሜሪካም ተመሳሳይ ፈቃድ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ገልፃለች፡፡

አሜሪካ የሱማሊላንድ ጎረቤት በሆነችው ጅቡቲ ውስጥ የባህር ሀይል ጦር ሰፈር ያላት መሆኑ ይታወቃል፡፡

ጅቡቲና ሱማሊላንድ ቀይ ባህርንና የኤደን ባህረ ሰላጤን በሚያገናኘው ባብ ኤልመንደብ ሰርጥ ላይ የሚገኙ ስትራቴጂያዊ አቀማመጥ ያላቸው አገራት ናቸው፡፡

ሱማሊላንድ ለአሜሪካ ይህንን መደራደሪያ ያቀረበችው ፕሬዝደንት ትራምፕ እምቅ ሀብት ካላቸው አገራት ጋር ጥብቅ ግንኙነት ለመመስረት ጥረት እያደረጉ ባለበት በዚህ ወቅት ነው፡፡

በቀረበው መደራደሪያ ፕሬዝደንት ትራምፕ ከተስማሙ ለሱማሊላንድ እውቅና መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates