መካከለኛ ምስራቅ
“እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ ሰፊ ግዛት እንዲኖራት መፅሐፍ ቅዱስ የሰጣት መብት አለ” ሲሉ የአሜሪካው አምባሳደር ገለፁ፡፡
የአምባሳደሩ 14 የሙስሊም ሀገራት "አደገኛና ፀብ አጫሪ አስተያየት ነው" ሲሉ ተቃወሙት፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 16/06/2018፡- የአረብና ሙስሊም ሀገራት በእስራኤል የሚገኙትን የአሜሪካ አምባሳደር አስተያየት አውግዘዋል።
አምባሳደር ማይክ ሁካቤ ባደረጉት ቃለ ምልልስ “እስራኤል በመካከለኛው ምሥራቅ ሰፊ ግዛት እንዲኖራት መፅሐፍ ቅዱስ የሰጣት መብት አለ” ብለዋል።
“ከግብፅ የአባይ ወንዝ እስከ ሶርያ እና ኢራቅ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ የግዛቷ አካል ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።
ሳዑዲ አረቢያ፣ ፓኪስታን፣ ቱርክና ጆርዳንን ጨምሮ ሌሎች አስር የሙስሊም ሀገራት “አደገኛና ፀብ አጫሪ አስተያየት ነው” ሲሉ የሁካቤን ንግግር ተችተውታል።
ሀገራቱ “የተመድን አለማቀፍ ህግ የሚጣረስ እና የጋዛን ጦርነት የሚያባብስ ነው” በማለት ተቃውመዋል።
የእስላማዊ ምክርቤት ትብብር (OIC) እና የገልፍ ትብብር ካውንስል (GCC) በጉዳዩ ላይ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።



