ሩሲያ ኬንያውያን በዩክሬን ውስጥ ለጦርነት መመልመላለች መባሉ አስተባበለች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/06/2018፡- በኬንያ የሚገኘው የሩሲያ ፌዴሬሽን ኤምባሲ በዩክሬን ግጭት ውስጥ ለመዋጋት የኬንያ ዜጎችን በመመልመል ላይ ሩስያ ተሳትፋለች የሚለውን ክስ ውድቅ አድርጓል፣ “አደገኛ እና አሳሳች የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ” ሲልም ገልፆታል፡፡
ትናንት የካቲት 12 በወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ኤምባሲው በኬንያ ሚዲያዎች፣ ወደ ሩሲያ ፌዴሬሽን የጦር ኃይሎችን ተቀለቅሎ በዩክሬን ጦርነት ዘመቻዎች ተሳትፈዋል የተባሉ የኬንያ ዜጎችን በተመለከተ በሕዝብ ላይ “ከፍተኛ ስጋት” ፈጥረዋል ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ከአንድ ሺህ በላይ ኬንያዊያን በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ለመዋጋት መመልመላቸው እየዘገቡ ነው፡፡
በድምሩ አንድ ሺህ የሚሆኑ ኬንያዊያን ለሩሲያ ለመዋጋት መመልመላቸውን የኬንያ የደኅንነት ሪፖርት በመጥቀስ ቢቢሲ ዘግበዋል።
ረቡዕ ዕለት ለአገሪቱ ምክር ቤት የቀረበው የኬንያ ብሔራዊ የደኅንነት አገልግሎት (ኒስ) ሪፖርት እስከ አውሮፓዊያኑ አዲስ ዓመት ድረስ 89 ኬንያዊያን በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ግንባር ላይ መሆናቸውን አስታውቋል።
በጦርነቱ ቢያንስ አንድ ኬንያዊ የተገደለ ሲሆን፤ ሌሎች በርካታ ዜጎች ደግሞ ቆስለው ወደ አገራቸው መመለሳቸው ገልጿል።
መጀመሪያ ላይ 200 የሚሆኑ ዜጎቹ በጦርነቱ ለሩሲያ ለመዋጋት ተመልምለዋል ብሎ የገመተው የኬንያ መንግሥት፤ ሞስኮ ኬንያዊያን ወታደሮችን መመልመሏል እንድታቆም ይፈልጋል።
ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ አባላት ያቀረቡት የምክር ቤቱ የአብላጫ ድምፅ መሪ የሆኑት ኪማኒ ኢችንጉዋ ሁኔታውን “በጣም የሚረብሽ” ሲሉ ገልጸውታል። የመንግሥት መኮንኖች መረብ ከሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ጋር በመሆን ኬንያዊያንን በመመልመል እና በጦርነቱ እንዲሳተፉ እያጓጓዝ ነው ሲሉም ከሰዋል።
ሪፖርቱ ግንባር ላይ ካሉት በተጨማሪ 35 ኬንያዊያን በሩሲያ የጦር ካምፕ ውስጥ መሆናቸውን፣ 39 ያህሉ መቁሰላቸውን እና 28ቱ ደግሞ መጥፋታቸውን ዘርዝሯል።
በምርመራው መሠረት ከ20 እስከ 50 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የቀድሞ የኬንያ ጦር አባላት፣ የቀድሞ የፖሊስ አባላት እና ሥራ አጥ ኬንያዊያን የምልመላው ዋና ዒላማ ናቸው ተብለዋል።
ምልምሎች 2,400 ዶላር ወርሃዊ ደሞዝ እንዲሁም ከ6,200 እስከ 8,300 ዶላር ጉርሻ ይከፈላችኋል ተብለው ቃል እንደተገባላቸውም ተጠቅሰዋል።


