
ኢትዮ ሚኒተር፡ 11/06/2018፡- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት በዚህ ሳምንት ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ጋር ውይይት ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን፣ ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የሚደረገውን ጥረት እንደሆነ ተመላክተዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ የቢሮው ከፍተኛ ባለስልጣን ኒክ ቼከር ሚኒስትሩን በአዲስ አበባ አግኝተው የኢኮኖሚ ትብብርን፣ የፀረ-ሽብርተኝነትን እና የቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ጨምሮ የጋራ ጥቅም ያላቸውን ዘርፎች ተወያይተዋል።
ኤምባሲው ሁለቱም ወገኖች አጋርነትን ማጠናከር እና በጋራ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ትብብርን ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በወጣው ጽሁፍ፣ ስብሰባው የኢኮኖሚ እድገትን፣ የደህንነት ተግዳሮቶችን እና የቀጠናው መረጋጋትን በመፍታት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተገልጿል።



