ኢራን፤ ኒውክሌርን በተመለከተ “በዋነኛ መርሆች” ላይ ከአሜሪካ ጋር መግባባት ላይ መደረሱን አስታወቀች፡፡

ኢትዮ ሚኒተር፡ 11/06/2018፡- ሁለቱ አገራት በጄኔቫ ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት ካደረጉ በኋላ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ፤ የኒውክሌር “ዋነኛ መርሆችን” በተመለከተ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል። አሜሪካም ደግሞ “በውይይቱ መሻሻል ታይቷል” ስትል ገልጻለች።
የአሸማጋይዋ ኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አልቡሳዲ “የጋራ ግቦችን በመለየት እና የቴክኒክ ጉዳዮችን በተመለከተ ድርድሩ ጥሩ መሻሻል ታይቶበታል” ብለዋል።
አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን “መሻሻል ቢኖርም ብዙ የምንወያይባቸው ዝርዝር ነጥቦች አሉ። የምንለያይባቸውን ነጥቦች በተመለከተ ኢራናውያን በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ምክረ ሐሳም ይዘው እንደሚመጡ ገልጸዋል” ሲሉ ስለ ድርድሩ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በበኩላቸው “አንዳንድ ጉዳዮችን በተመለከተ ድርድሩ በጥሩ ሁኔታ ተካሂዷል። ፕሬዝዳንቱ ቀይ መስመር ብለው ያስቀመጧቸው እና ኢራናውያን ገና ያልተቀበሏቸው ነጥቦችም አሉ” ሲሉ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ ግን የኢራኑ ፕሩዝዳንት አያቶላህ ኻሜኒ “የዓለም ኃያሉ ሠራዊት መልሶ እንዳይነሳ ሆኖ ሊመታ ይችላል” ሲሉ አስጠነቀቁ፡፡
የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ “የዓለም ኃያሉ ሠራዊት መልሶ እንዳይነሳ ሆኖ ሊመታ እንደሚችል” በመግለጽ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምላሽ ሰጡ።
በኢራን ዙሪያ የጦር መርከቦቿን እያስጠጋች ያለቸው አሜሪካ፤ ኢራን የሚቀርቡላትን ቅድመ ሁኔታዎች በመቀበል ከስምምነት ካልደረሰች እርምጃ እንደሚወሰድባት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሲዝቱ ቆይተዋል።
ይህንን በተመለከተ ኻሜኒ በሰጡት ምላሽ “የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሠራዊታቸው በዓለም ላይ ጠንካራው እንደሆነ በተደጋጋሚ ይናገራሉ። ጠንካራ የተባለ ሠራዊት አንዳንድ ጊዜ እንዳይነሳ ተደርጎ ክፍኛ ሊመታ ይችላል” በማለት አስጠንቅቀዋል።
ጠቅላይ መሪው ጨምረውም አሜሪካ የጦር መርከቦችን ወደ ኢራን መላኳን በተደጋጋሚ እየገለጸች መሆኗን በመጥቀስ “መርከቦች አደገኛ መሣሪያዎች ናቸው፤ ነገር ግን የበለጠ አደገኛው ነገር እነዚህን መርከቦች ከባሕር ሥር እንዲሰምጡ የሚያደርገው የጦር መሣሪያ ነው” በማለት የአሜሪካ መርከቦች የሚገጥማቸውን ምላሽ አመልክተዋል።



