የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያን ባንዲራ እና መሪዎችን የሚያንቋሽሹ ምስሎችን በማሳየቱ ከፍተኛ ቁጣ አስነሳ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/06/2018፡- በፀረ-ኢትዮጵያነቱ የሚታወቀው የሻአቢያ አገዛዝ ለኢትዮጵያ ያለውን ጥላቻ የሚያንፀባርቅ ድርጊት በድጋሚ ፈጽሟል ተብለዋል።
በዚህ ሳምንት በምፅዋ ወደብ ባዘጋጀው “የፈንቅል ኦፕሬሽን” 36ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ከሚቀርቡት ኤግዚቢሽኖች አንዱ የጥበብ ኤግዚቢሽን ነበር።
በስዕሉ ላይ በግልጽ እንደሚታየው አንድ ወታደራዊ ጫማ የለበሰ ሰው የኢትዮጵያን አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ባንዲራ ረግጦ ይታያል።
ከዚህ በተጨማሪ ፎቶው የአፄ ኃይለ ሥላሴን፣ የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን፣ የቀደምው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድን የቁም ስዕሎች ሲረግጥ ያሳያል።
ፎቶው በከፍተኛ የሻአቢያ ባለስልጣናት የተጎበኘ ከመሆኑ በተጨማሪ በኤርትራ መንግሥት ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ ላይ ተለጥፎ የሚገኝ መሆኑን አገዛዙ ለጎረቤት አገር ያለውን ንቀት እና ጥላቻ እንደሚያሳይ በብዙዎች እየተጩት ይገኛሉ።
የኤርትራ ሰራዊት በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንደሚገኝ እየተገለፀ ሲሆን ስርዓቱ ሰራዊቱ እንድያስወጣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት በላከው ደብዳበ መጠየቁ ይታወሳል፡፡
በኢትዮጵ ባንዴራ መረገጥ ዙሪያ እስካሁን ከኢትዮጵያ መንግሥት ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫ አልወጣም።
በሁለቱም አገራት የተፈጠረውን መቃቃር ከፍተኛ ደረጃ መድረሱ እየተገለጸ ባለበት ወቅት የኤርትራ መንግስት እንደዚህ ዓይነት አፀያፊ ተግባር መፈፀሙ ሁኔታዎች ሊባብሱ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት ተፈጥረዋል፡፡



