ማህበራዊ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሁለት ዓመታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሱዳናዊያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ሲል አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/06/2018፡- እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) መረጃ ከሆነ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ከጎረቤት አገሮች ከ529,000 በላይ ስደተኞች ወደ ሱዳን ተመልሰዋል።
ኤጀንሲው ከጥር 2024 እስከ ታህሳስ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ሱዳን የተሻገሩ 529,661 ሰዎችን መመዝገቡን አስታውቋል።
ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ በሱዳን ጦር እና በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች መካከል በተቀሰቀሰ ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በአገር ውስጥ ተፈናቅለዋል፤ ወደ ጎረቤት አገሮች ተሰድዋል፡፡
ጦርነቱ በዓለም ላይ ካሉት እጅግ የከፋ የሰብአዊ ቀውስ አንዱ ብሎ የገለጸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ እስካሁን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን እና ወደ 13 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውን ሪፖርት አድርጓል።
ከተመለሱት ስደተኞች ውስጥ 89 በመቶ የሚሆኑት ከግብፅ የተመለሱ መሆናቸው የጠቆመው የዓለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት ሪፖርት ከቻድ የተመለሱት ግን ከ11 በመቶ ያነሱ ናቸው። በቁጥር ያነሱት ደግሞ ከኢትዮጵያን ጨምሮ ከሌሎች አገሮች እንደተመለሱ አስታውቀዋል፡፡



