አፍሪካ

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ የሱፍ ከግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድር አብደላቲ ጋር በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ ጉባኤ ላይ መወያየታቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/06/2018፡-  ውይይቱ በግብፅ ሰኔ 2026 በሚካሄደው 8ኛው የመካከለኛው ዓመት የማስተባበሪያ ስብሰባ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ሲሆን ከአፍሪካ የንግድ ፎረም ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ መድረክ ነው።

ሁለቱ አመራሮች ህብረቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች የሚያራምዱ ተጨባጭ ውጤቶችን በማረጋገጥ ላይ ሐሳብ ተብሏል።

ሊቀመንበሩ መሐሙድ አሊ የሱፍ ግብፅ በአህጉሪቱ ሰላምን፣ ደህንነትን እና ዘላቂ ልማትን በማሳደግ ረገድ የምታደርገውን ቀጣይ ጥረት አድንቀዋል።

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤው ስኬታማ አደረጃጀትን እና ውጤታማ አፈፃፀምን ለማረጋገጥ ከግብፅ መንግስት ጋር በቅርበት ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነትም ማረጋገጣቸው የህብረቱ መረጃ ያሳያል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates