አፍሪካ

የሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ጋር መወያየታቸው ታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/06/2018፡- የሳዑዲ አረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አብዱልከሪም አል ካሪጅ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህ ጋር በአሥመራ ተገናኝተው መወያየታቸው ተገለፀ።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ከሳዑዲ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር የተገናኙት ሐሙስ የካቲት 5/2018 ዓ.ም. መሆኑን የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር በይፋዊ የኤክስ ገጹ ላይ ይፋ አድርጓል።

የሳዑዲ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢንጂነር ማሌን ቢን አብዱልካሪም አል ካሬጂ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ሁለቱ አገራት ያላቸውን ወዳጅነት እና ትብብር ለማጠናከር መነጋገራው ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ የሳዑዲ ልዑካን ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ጋር በቀጠናው እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል።

በዚህ ሳምንት አጋማሽ ላይ የሳዑዲ አረቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሐን ወደ ኢትዮጵያ በማምራት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በአዲስ አበባ በሁለትዮሽ እንዲሁም ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው ይታቀሳል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የሳዑዲው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ውይይት በዝርዝር ባይገለጽም “በቁልፍ ዘርፎች ላይ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር” እንዲሁም “የሁለቱም አገራት ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መተባበር” ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል።

የሳዑዲ አረቢያ ልዑክ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ጋር “በቀይ ባሕር ዙሪያ የሚገኙ አገራት ተለዋዋጭ በሆነው ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች እና አዝማሚያዎች ባሻገር የአካባቢውን ሰላም እና ደኅንነት በማረጋገጥ ረገድ ስለሚኖራቸው አስተዋጽኦ ተነጋግረዋል” ተብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates