ኢትዮጵያኢኮኖሚ

ኢትዮጵያ በቢሾፍቱ የምታስገነባው ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ምዕራፍ መጀመሩ ተገለፀ፡፡

በሌላ በኩል የኢ/ያ አየር መንገድ በመንፈቅ ዓመቱ 4.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳገኘ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 03/06/2018፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባውን አዲሱንና ግዙፉን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ  የግንባታው ሂደት በይፋ መጀመሩን ወርልድ አርክቴክቸር ዘግቧል።

ይህ 6 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ሜጋ ፕሮጀክት በዋናነት በብድር በሚገኝ ፋይናንስ የሚከናወን ሲሆን፣ ሲጠናቀቅም በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንደሚኖረው መገለፁ ይታወሳል።

አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምስራቅ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በቢሾፍቱ አካባቢ 35 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ባለው ቦታ ላይ የሚያርፍ ሲሆን፣ የመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ በፈረንጆቹ 2029 ተጠናቆ 60 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ እንደሚጀምር ታውቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት፣ አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በሥራ ላይ ሲውል የአሁኑ የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት አይቆምም፤ ይልቁንም ለሀገር ውስጥ በረራዎች፣ ለቪአይፒ አገልግሎቶችና ለቀጣናዊ በረራዎች ትኩረት ሰጥቶ አገልግሎቱን ይቀጥላል ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እአለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግማሽ ዓመቱ 4.4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታውቀዋል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ሦስት አዳዲስ ዓለም አቀፍ የበረራ መዳረሻዎች ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፣ ይህም አየር መንገዱ የሚበርባቸውን የዓለም ከተሞች ቁጥር 145 እንዲደርስ አስችሎታል።

አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ የአውሮፕላኖቹ ብዛት 147 መድረሱነ በግማሽ ዓመቱ ውስጥ 10.6 ሚሊየን መንገደኞችን ማጓጓዝ መቻሉን ተመላክቷል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates